መንፈሳዊ አገልግሎቶች
1. ሳምንታዊ መደበኛ የኪዳን እና ቅዳሴ ፀሎት አገልግሎት
ይህ መደበኛ የጸሎት አገልግሎት ሲሆን ቅዳሜ ከ ጠዋቱ 7:00 am እስከ 9:00 am ፣ እሁድ ከ ጠዋቱ 4:00 am እስከ 12 pm ፣ እንዲሁም በስራ ቀናት ወር በገባ 5, 12, 21, 23, እና 29 የኪዳን ጸሌት አገልግሎት ከጠዋቱ 7:00 am – 9:00 am ሰዓት ይሰጣል።
2. አመታዊ የንግስ በዓላት
በቤተክርስቲያናችን ጥምቀትን ጨምሮ አምስት የአመታዊ ንግሰ በዓላት ይካሄዳሉ። በዚህም ወቅት አብዛኛውን የቤተክርስቲያኒቱ ተገልጋዩች እንዲሁም እንግዶች ከተለያዩ የሚኒሴታ እስቴት በዓሉን ለመታደም ይገኛሉ። አገግሎቱም ከዋዜማ 4:00 pm – 6:00 pm ፣ ነጋታው 1:00 am – 12:00 pm ድረስ ረዘም ላለ ጊዜ የጸሎትና የምስጋና አገልግሎት ይሰጣል።
3. የጥምቀት (የክርስትና) አገልግሎት
ይህ አገልግሎት ሰዎች ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ዳግመኛ የሚወለዱበት፣ የስላሴ ልጅነት የሚያገኙበት አገልግሎት ነው። ወንድ በተወለደ በ 40 ቀኑ ሴት በተወለደች በ 80 ቀኗ እንዲሁም ማንኛውም ሃይማኖቱን የሚቀበል ምእመን በሚቀበልበት እድሜ የሚሰጥ ልዮ ስርዓትና አገልግሎት ነው።
4. የፍትሃት አገልግሎት:
የፍትሃት አገልግሎት በህይወት ለተለዩ ምዕምናን የሚደረስ ወይም የሚደረግ የመታሰቢያ ጸሎት ነው።
5. የጸበል አገልግሎት (Holy water healing service)
ይህ የጸበል አገልግሎት ለታመሙ ሰዎች ፈውስን ለጤነኞች መንፈሳዊ ብርታትን የሚሰጥ አገልግሎት ሲሆን በዋናነት በቤተክርስቲያናችን ጸበል ቤት የሚሰጥ ነው። ምእመናን ልጅ ከወለዱ በኋላ ካህናት እቤታቸው በመሄድ የጸበል አገልግሎትም ይሰጣል።
6. አመታዊ የመስቀል እና ደመራ በዓል
ይህ በዓመት አንድ ጊዜ መስከረም መጨረሻ ላይ የሚከበር በዓል ሲሆን፣ የክርስቶስ መስቀል መገኘትን የሚተርክና የሚዘክር በዓል ነው። ይህ በዓል ከ2021 ጀምሮ በካስኬድ ፓርክ እየተከበረ የቆየ ሲሆን ከበዓሉ አከባበር እና ድምቀት የተነሳ ከሃይማኖታዊ ገጽታው በተጨማሪ በበርካታ የሮችስተር ነዋሪዎችና የህዝብ ተወካይ ኃላፊዎችም ተገኝተውበታል። በ 2023 መስከረም ባከበርነው ደማቅ በዓል ላይ የ ሮችስተር ከተማ ከንቲባ Mrs. Kim Norton (Mayor ) እና በርካታ ታዳሚዎች በመገኘታቸው የአማኙ ህዝብ ስሜት በደስታ ተሞልቶ ታይቶዋል ::
7. የጋብቻ ስርዓት አገልግሎት
ቤተክርስቲያናችን በኦርቶዶክሳዊ የጋብቻ ህግና ደንብ መሰረት ለሁለት ጊዜ የተሟላ የተክሊን ጋብቻን ያስፈፀመ ስሆን በከተማችንም በተለያዩ የጋብቻ የቀለበት ስነ ስርዓት ላይ በመገኘት ፁሎት በማድረግና የጋብቻን ምንነት ላይ ትምህርት ስትሰጥ ቆይታለች ወደፊትም ይህን ዘርፍ በማጠናከር ወጣቶች ጋብቻቸውን በቤተክርስቲያን እንዲፈፅሙ ምክር ትለግሳለች::
የህፃናት እና የታዳጊዮች ምክርና የመንፈሳዊ ሁለገብ ትምህርት አገልግሎት
ማንኛውም ወላጅ ልጁ በሃይማኖታዊ እና በማህበራዊ ግብረገብነት ታንፆ በዲስፕሊን እንዲያድግለት ይፈልጋል : ለዚህ ለህፃናት መልካም አስተዳደግ የመጀመሪያው ዐቢይ ነገር ፈርሐ -እግዚአብሄርን በአእምሮቸው ውስጥ ማስረፅ ነው :: ለዚህም የቤተክርስቲያን አስተዳደርና የሰንበት ትቤት ወሳኝ ሚና ሊጫወቱ ይገባል : ይህ በአሁኑ ደካማ የአገልግሎት ዘርፍ በመሆኑ በሚቀጥሉት መጪ አመታት አሁን እንደተጀመረው የድቁና ትምህርትስልጠና የምሰጥበትና የሚካኑበት ይሆናል ታዳጊዎቹ ከውጪው የማህበራዊ አገልግሎትና ተሳትፎ ውጭ እንዳይሆኑ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ አገልጋይ ሙያተኞችን በመጋበዝ እንዲማሩና የህዝቡ አካል ሆነው እንዲያድጉ ይደረጋል :: በዚህ ክረምት (ሳመር 2024) ሁለት የተላያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ተጀምረዋል። አንደኛ ለተወሰኑ ህፃናት የድቁና ትምህርት የተጀመረ ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ ለሁልም ህፃናት ያካተተ የቋንቋነ የሃይማኖት ትምህርት ተጀምረዋል።
ማህበራዊ አገልግሎቶች
1. የምክር አገልግሎት
2. የዕድሜ ባለፀጋ የሆኑትን አባቶችንና እናቶችን መጎብኘት መርዳት:
3. የታመሙትን ማበረታታት መጠየቅ
4. በሃዘን ጊዜ የተጎዱ ቤተሰቦችን ማፅናናትና ማገዝ :
የቤተ ክርስቲያናችን አገልጋዮች ካህናት እና ዲያቆናት

መላከ ገነት ቀሲስ ፀሓይ ጌታሁን – የደብሩ አስተዳዳሪ

ሊቀ ጠበብት ይባቤ – የደብሩ መሪ ጌታ እና የአብነት መምህር

መጋቤ ሥርዓት ቀሲስ ወርቁ – የደብሩ ካህን እና የወንጌል መምህር






