Departments

Back to Home page

ሰበካ ጉባኤ አስተዳደር (Board Members)

አላማ

ቅድስት ቤተክርስቲያን ዘመናዊ መዋቅር ያላት ሆና እንድትተዳደር በተደነገገው ህግ ቃለ ዓዋዲ መመስረት ጋር አብሮ የተጀመረ መንፈሳዊ ጉባኤ ነው። ሰበካ ጉባኤ በቃለ አዋዲ አንቀፅ 5 መሰረት የሚከተሉት አለማዎች አሉት:

  • ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለመጠበቅና አገልግሎቷም የተሟላ እንዲሆን ለማድረግ
  • የቤተክርስቲያንን አገልጋዮች ሐዋርያዊ ተግባር ለማደራጀትና እንደዚሁም ችሎታቸውንና ኑሮአቸውን ለማሻሻል
  • ምዕመናንን ለማብዛት እንደዚሁም በመንፈሳዊ ዕውቀት ጎልምሰው በምግባርና በሃይማኖት ጸንተው በክርስቲያናዊ ህይወት እንዲኖሩ ለማድረግ
  • የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደር ለማሻሻልና በማናቸውም ጉዳይ ራሷን ለማስቻል ነው

አባላት

መላከ ገነት ቀሲስ ፀሓይ ጌታሁን – የደብሩ አስተዳዳሪ

ዶክተር ብሩህዓለም ታዬ – ምክትል ሰብሳቢ

❖  ወርቅነህ ደመወዝ – ጸሓፊ

ጌታሁን ምትኩ – ሒሳብ ሹም

ቤዛነሽ ውበቱ – ንብረትና ግምጃ ቤት ተወካይ

ፋንታ ወልደገብርኤል – ገንዘብ ያዥ

ስብከተ ወንጌል | Sermons

ስብከት “ሰበከ፤ አስተማረ” ከሚለው የግእዝ ግሥ የመጣ ሲሆን፣ በጌታ የታዘዘ፣ የእግዚአብሔርን ቃል መናገር፣ ወንጌልን ለዓለም መስበክ፣ ያላመኑትን ለማሳመን መናገር፣ የክርስቶስ ምስክር መሆን ማለት ነው። (መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ ፸፬)

Click here to learn about the Beliefs and Teachings of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church

ሰንበት ት/ቤት (Sunday School)

እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ልጅ በአርያውና በአምሳሉ ከፈጠረ በኋላ ሰው ከፈጣሪው ጋር በጥብቅ እንዲናገናኝ ልዩ ልዩ የአገልግሎት መንገዶችን አዘጋጀ። እያንዳንዱ በተሰጠው መክሊት ያተርፍና በጸጋው ያገለግል ዘንድ በመጀመርያ ዕድሜው በፈቀደለት ሁሉ መማርና ማገልገል ይኖርበታል። እግዚአብሔር አምላክ መመለክ በአለበት አግባብ ለማምለክ እምነት ያስፈልጋል፤ ከእምነት እንዳንወጣ ደግሞ ስለምናምነው ነገር በቂ ዕውቀት ሊኖረን ይገባል፤ እምነትን፣ ተስፋና ፍቅርን ሰንቆ እስከመጨረሻ ድረስ ለመጽናት መንፈሳዊ ዕውቀት መሠረታዊ ነው።

የሰንበት ትምህርት ቤት ዓላማ፦

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዶግማ፣ ቅኖና፣ እምነትና ሥርዓት ተጠብቆ ሳይበረዝ ሳይከለስ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ
  • ማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታይ የሆነ ምእመን የሃይማኖቱን ሥርዓት በውል እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ
  • ወጣቶች የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት ተምረው ለሀገርና ለወገን ጠቃሚ፣ መልካምና በሥነ ምግባር የታነፁ ዜጎች እንዲሆኑ ማድረግ
  • በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ (መክ. ፲፪፡፩) የሚለውን የአምላክ ተእዛዝ ወጣቶች እንዲፈጽሙ ማስቻል

Hours

Saturdays 6 am – 9 am

Sunday 4 am -12:00pm

Address:

804 E Center St, Rochester, MN 55904

st.georgeethiopianorthodoxtc@gmail.com