About us

Back to Home page

ታሪካዊ አመጣጥ(አጀማመር)

የቤተክርስቲያናችን አመሰራረት (how the church started) 

የሮችስተርና አካባቢው የደብረ ገነት ቅዱስ ጊዩርጊስ እና አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን በአሜሪካ ከሚገንኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናት  መካከል አንዱ ሲሆን በሮችስተር ሚኒሶታ ከተማ ከተመሰረተበት  ከ2004 ዓመተ ምህረት ጀምሮ  እስከ አሁን ድረስ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

የዚህ ቤተክርስቲያን ምስረታ  ጥንስሱ የተጀመረው 15 ባልበለጡ ነዋሪዎች በአፓርትሜንት መኖሪያ ክፍል ውስጥ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት በማድረግ ነበር :: ይህ በ2004 በጥቂቶች በተጀመረው የጥናት ፕሮግራም ላይ የተወሰኑ ስዎች በመጨመራቸው ለቦታው አመቺነት ሲባል የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የክፍል ጥያቄ ቀርቦላቸው የቤተርስቲያናቸውን የሰንበት ት/ቤት አዳራሹን እንድንጠቀምበት በመፍቀድ በቤተክርስቲያናቸው ያለምንም ችግር እስከ 2013 ዓም ለ9 ዓመታት ስንጠቀምበት ቆይተናል ።

በቆይታችንም ሆነ እስከ ዛሬ ለደረስንበት የዕድገት ደረጃ የሮችስተር ግሪክ ቤተክርስቲያን  ውለታ የማይረሳ አሻራን አሳርፎብናል:: ያም በመሆኑ ይኸው ዛሬ አሁን የምንገለገልበትን ቤተክርስቲያን ገዝተን ለ11 ዓመታት እየተገለገልንበት እንገኛለን :: ለደረስንበት የእድገት ደረጃ የሚኔያፖሊስ እና የሲፎልስ ኦርቶዶክሳዊ ምዕመናንና አስተዳደራቸው የሚረሱ አይደሉም።

    አሁን ባለንበት የአገልግሎት ወቅት የምዕመናን ቁጥር ወደ 165 ከመድረሱም በላይ የአገልግሎት ዘርፉም እንደዚሁ እየጨመረ በመምጣቱ አገልግሎቱ በክፍል ጥበት ምክንያት የተፈለገውን ያህል አገልግሎት መስጠት አልቻለም :: ይህም በመሆኑ የቤተክርስቲያናችን የሰበካ ጉባዔ ኮሚቴ ችግሩን ለመቅረፍ የሰላምና የልማት ንዑስ ኮሚቴ በማዋቀር ንዑስ ኮሚቴው ቤተክርስቲያን ለመግዛት ወይም ለማሰራት በከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል::

Hours

Saturdays 6 am – 9 am

Sunday 4 am -12:00pm

Address:

804 E Center St, Rochester, MN 55904

st.georgeethiopianorthodoxtc@gmail.com